Telegram Group Search
ቅርጫ አልተከለከለም‼️

አ/አ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዉ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክልከላ ያልተደረገ ሲሆን በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

የከተማችን ነዋሪ በአላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ዉስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልክታችንን እናስተላልፋለን።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 907 ቤቶችን ለነዋሪዎች አስተላለፈ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ለኑሮ አመቺ ያልነበሩ አፍርሰን በአጭር ጊዜ መልሰን የገነባናቸውን እና ያደስናቸውን 907 ቤቶች እንኳን ለትንሳኤ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለን ለነዋሪዎች አስተላልፈናል ብለዋል።
በተጨማሪም አዳዲስ ግንባታዎችን በዛሬው ዕለት እንዳስጀመሩ ነው የገለጹት፡፡

አርጅተው በመፍረስ ላይ የነበሩ ጎስቋላ ቤቶችን አፍርሰን ለዘመናዊ አኗኗር አመቺ በሆነ መልክ በነበሩበት ቦታ ላይ መልሰን የገነባነው በርካታ ልበቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ነው ብለዋል ከንቲባዋ።

የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል ለወገኖች በመድረስ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ የከተማዋ ባለሃብቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ነዋሪዎች እድሉ ተጠቃሚ ስለሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ከንቲባዋ ፥ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት አዲስ አበባን የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ‼️

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያን እና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአረጋዊያን እና ለአቅመ ደካሞች የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ማጋራታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
[CREATINE MONOHYADRATE ]

ጡንቻን ለመገንባት እና ጉልበት ለማግኘት፤ ለሰውነትዎ የሚያስፈልገውን ይስጡት!

በፆም ወቅት የሚወሰድ!

ጥንካሬ፣ብርታት እና ፈጣን የሰዉነት ጥገና ያስፈልገኛል ብለዉ ካሰቡ ክሬቲን ይገባዎታል
👨🏾‍⚕️የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት እንደሚያሳየዉ ክሬቲን የሚጠቀሙ አትሌቶች እና ስፓርተኞች 23 % የተሻለ አፈጻጸም እና ጥገና ያሳያሉ!🏃‍♂️

ለነፃ የምክር አገልግሎት እና የተሟላ መረጃ ወደ ጥሪ ማእከላችን ይደውሉልን
☎️9369 ☎️

አድራሻ📍 አዳማ - ፖስታ ቤት ሶሬቲ ህንፃ ፊትለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል 1ኛ ፎቅ ሱቅ ቁጥር 110

☎️ +251966113766 ☎️

Join https://www.tg-me.com/+RCaZ_Ka6SOrlz0u5
የእስራኤል ካቢኔ የኳታሩ የቴሌቪዥን ጣቢያ አልጀዚራ ቢሮ እንዲዘጋ ወሰነ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ካቢኔው በእስራኤል የሚገኘው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቢሮ እንዲዘጋ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን አስታውቋል።

ውሳኔው የቴሌቪዥን ጣቢያውን የስርጭት ቁሳቁሶች መውረስ እና የተቋሙን ድረገጽ መዝጋት ያካትታል ተብሏል።

እስራኤል ከዚህ ቀደም በጋዜጠኞች ላይ በተናጠል ካሳለፈችው እገዳ ውጭ የውጭ የመገናኛ ብዙሃን እንዲዘጋ ስትወስን አልጀዚራ የመጀመሪያው ይሆናል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን ኢሰማኮ አስታወቀ‼️

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለዉ ደመወዝ ክፍያ ኑሮን መቋቋም ባለመቻላቸው ለችግር መጋለጣቸውን በመግለፅ ይህን አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ያቀረብኩት ጥያቄ ትኩረት ሳይሰጠዉ ቀርቷል ብለዋል።

ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበው ምላሽ አላገኙም ካሏቸዉ ጥያቄዎች ዉስጥ "ሠራተኞች አሁን እየተከፈላቸው ባለው የደመወዝ ክፍያ የኑሮ ዉድነቱን በፍጹም መቋቋም ያልቻሉ በመሆኑ ደመወዝ የገቢ የሥራ ግብር እንዲቀነስ ላቀረብነዉ ጥያቄ መንግሥት ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ብሏል።

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ የተደነገገ ቢሆንም የደመወዝ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ በሚንስትሮች ምክር ቤት ባለመውጣቱ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያልተገባ መሆኑን ነዉ ማህበሩ ያስታወቀው።

በጦርነት ዘላቂ መፍትሒ ስለማይመጣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ግጭትና ጦርነት ቆሞ በዉይይት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁሉም ወገኖች በድርድር እንዲፈቱ የጠየቀው ኢሰማኮ ለጉዳዩ አፅንኦት ይሰጠዉ ብሏል በመግለጫው።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የህወሓት ኃይሎች" ከሱዳን ጦር ጎን በቅጥረኝነት ተሰልፈው ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር እየተዋጉ ነው መባሉን አስተባብሏል‼️

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ባለፈው ቅዳሜ የህወሓት ኃይሎች ከሱዳን ጦር እና ተባባሪ ሚሊሻዎች ጋር ሆነው እየተዋጉት እንደሆነ ማረጋገጡን መግለጹን ተከትሎ ነው።

የሱዳን ጦርነት ከተጀመረበት ከሚያዝያ 2023 ወዲህ የሱዳን ጦር የውጭ ቅጥረኞችን እርዳታ እየፈለገ ነው የሚል ክስ ያቀረበው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር፣ በጦርነት ወቅት ተገድለው የተገኙ ቅጥረኞችን መመዝገቡን ጠቅሷል።

የህወሓት ኃይሎች ከሱዳን ጦር ጎን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው የሚለውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች "መሰረተቢስ ክስ" በጽኑ እንደሚያወግዝ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ታግታ የተወሰደችው የ2 ዓመት ከ8 ወር ህፃን በተደረገ የተቀናጀ ክትትል በሦስት ቀናት ውስጥ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ‼️

ታግታ የተወሰደችው የ2 ዓመት ከ8 ወር ህፃን የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ጠንካራ ክትትል በሦስት ቀናት ውስጥ መገኘቷን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። 

የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳንኤል የተባለችው ህፃን የታገተችው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሳርቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተወስዳ እንደነበር ተጠቅሷል።

ቸርነት ጥላሁን የተባለው ተጠርጣሪ ከቤተሰቡ ጋር በነበረው ቅርበት ሕፃን አቢጊያን በተለያዩ ቦታዎች እየወሰደ በማዝናናት እንደ ቤተሰቡ አባል ያጫውታት እንደነበረና ከአምስት ወር በላይ ከቤተሰቡ ጋር በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የነበረው ቅርርብ ወንጀሉን በቀላሉ ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለትም ነው ፖሊስ የገለፀው።

ግለሰቡ ሚያዝያ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ስዓት ተኩል ገደማ ወደ ህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት በመሄድና "እናቷ አምጣት ብላኛለች" ብሎ ለቤት ሰራተኛዋ ከነገረ በኋላ ሕፃኗን ወስዶ በማገት ገንዘብ እንዲሰጠው ከወላጆቿ ጋር ሲደራደር መቆየቱን ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪው 150ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንዲሰጠው በመጠየቅ ገንዘቡን ማግኘት ካልቻለ ሕፃኗን በህይወት እንደማያገኟት ሲዝት እንደነበረ የህፃን አቢጊያ ወላጅ እናት ለፖሊስ በሰጠችው ቃል ማስረዳቷም ነው ፖሊስ የጠቀሰው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህፃኗን ለማስመለስና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ቀንና ለሊት ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ በተደረገው ክትትልም ትናንት ሚያዚያ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አለም ሰላም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠርጣሪው ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለሶስት ቀናት ያህል ታግታ የቆየችው ህፃን አቢጊያ ዳንኤል  ልትገኝ መቻሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ህፃናት ልጆች ለእንደዚህ አይነት ወንጀል ተጋላጭ እንዳይሆኑ እንዲጠብቋቸው አደራ የተሰጣቸው ግለሰቦችም ሆኑ ሞግዚቶችና ወላጆች  ነገሮችን በጥርጣሬ በማጤንና የማረጋገጥ ሃላፊነታቸውን በመወጣት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ቦሌ አየር መንገዱ ይቅርታ ጠየቀ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ዛሬ ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ የታየ ቢሆንም አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገዶኞቻችንን ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ወርደዋል። በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ውድ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
[CREATINE MONOHYADRATE ]

ጡንቻን ለመገንባት እና ጉልበት ለማግኘት፤ ለሰውነትዎ የሚያስፈልገውን ይስጡት!

ጥንካሬ፣ብርታት እና ፈጣን የሰዉነት ጥገና ያስፈልገኛል ብለዉ ካሰቡ ክሬቲን ይገባዎታል
👨🏾‍⚕️የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት እንደሚያሳየዉ ክሬቲን የሚጠቀሙ አትሌቶች እና ስፓርተኞች 23 % የተሻለ አፈጻጸም እና ጥገና ያሳያሉ!🏃‍♂️

ለነፃ የምክር አገልግሎት እና የተሟላ መረጃ ወደ ጥሪ ማእከላችን ይደውሉልን።

አድራሻችን;- ሆሳዕና ጮራሞ ሕንፃ 1 ፎቅ የቤት ቁጥር 07 ጎራ በማለት የሚፈልጉትን ያገኛሉ።

☎️ +251966114766 ☎️

☎️ 9369 ላይ ይደውሉ   ☎️
መኪና ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ከፈለጉ ያለምንም ክፍያ
ይህንን የቴሌግራም መተግበሪያ ይቀላቀላሉ።

https://www.tg-me.com/Poppycarmarket

☎️ 0911407105   👈 ይደውሉልን
የእስራኤል ጦር በጋዛ እና ግብጽ መካከል ያለውን ወሳኝ ማቋረጫ በመቆጣጠር ወደ ራፋ ከተማ እየገሰገሰ ነው ተብሏል‼️

አለምአቀፍ አደራዳሪዎች፣ እስራኤል እና ሀማስ ተኩስ ለማቆም እንዲስማሙ ጥረት እያደረጉ ባለበት ወቅት የእስራኤል ጦር በጋዛ እና ግብጽ መካከል ያለውን ወሳኝ ማቋረጫ በመቆጣጠር ወደ ራፋ ከተማ እየገሰገሰ ነው ተብሏል።

ሀማስ፣ እስራኤል ጥቃት በመክፈት በካይሮ እየተካሄደ ባለው የተኩስ አቁም ድርድር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረች ነው ሲል ከሷል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
2024/05/08 15:16:08
Back to Top
HTML Embed Code: